

የ”ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢኒሼቲቭ” (The great green wall initiative) የባለሙያዎች እና የአጋር አካላት ላይ ያተኮረ ስብስባ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት መካሄድ ጀምሯል።
በስብሰባው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን አመራሮች፣ የአባል አገራት ተወካዮች፣ ባለሙያዎች፣ የልማት አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
እስከ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው ስብሰባ የኢኒሼቲቩ ስትራቴጂ እና የትግበራ ማዕቀፍ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።
የኢኒሼቲቩን አፈጻጸም በመገመግም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎም ይጠበቃል።
እ.አ.አ በ2007 የተጀመረው “ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢኒሼቲቭ” በረሀማነትን ለመከላከል 8 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ደን በሳህል ቀጣና ለመትከል ያለመ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
