




በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞን ማዕከል ፐብሊክ ሰርቫንት የአራተኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
በመድረኩ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እና የፓርቲያችን ብልፅግናን ተቋማዊ አሰራር ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ኮፍረንሶች ወቅታቸውን ጠብቀው መካሄድ የሚገባቸው መሆኑ ተናግሯል።
አቶ በድሉ አያይዘውም የብልፅግናን እሳቤ በአግባቡ የተረዱ ጠንካራ አባላትን ለመፍጠር የአደረጃጀት መመሪያን በጠበቀ መልኩ ኮንፍረንሶችን በአሰራር ስርዓት መሰረት ማካሄድ እንደሚገባ ጠቅሶ የፓርቲን አሰራር ማጠናከር የሁሉም አባላት ድርሻም እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በኮንፍረንሱም ላይ የ2017 በጀት ዓመት የአስተዳደር ዘርፍ የማህበራዊ ዘርፍ እና የኢኮኖሚ ዘረፍ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው እየተገመገመ ይገኛል።
የፓርቲ ስራዎችን በማጠናከር ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት አባላት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆናቸው ተገልጿል።
በመድረኩ በቀጣይ ጠንካራ የሆነ ሥራዎች ማጠናከር እና ክፍተቶች ለማረም እና የ2018 የእቅድ አካል ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
