የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ የሥራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ የስራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ጉባዔ በታርጫ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዳውሮ ዞን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ዳዊት ሚኖታ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫዎች መሆናቸውን አንስተዋል።

በተጨማሪ የዞኑ ምክር ቤት በተጠናቀቀው የበጀት አመት በርካታ ውጤታማ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንም ገልፀዋል።

ጉባዔው ለተከታታይ 2 ቀናት የሚካሄድ መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በዚህም 7 የተለያዩ አጀንዳዎች የሚነሱ ሲሆን፤የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድ የሚቀርብ ይሆናል።

በጉባኤው የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫ፣የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁና የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ዳዊት ሚኖታን ጨምሮ ሌሎች የዞን እንዲሁም የወረዳዎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *