




በካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የዞን ማዕከል ፐብሊክ ሰርቫንት የ2017 ዓ/ም 4ኛ ዙር ማጠቃለያ የአባላት ኮንፈረንስ በኢኮኖሚ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ዘርፍ ህብረቶች ተካሂዷል ።
በኢኮኖሚ ቁጥር 1 እና 2 ዘርፍ ህብረቶች በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል ።
የተጀመሩ አገራዊ እድገትና ብልጽግና ጉዞን እውን ለማድረግ የፐብሊክ ሰርቫንቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑ በኮንፈረንሱ ተገልጿል ።
በ2017 በጀት ዓመት በየህብረቱ የተሰሩ መልካም ነገሮችን በማጠናከር የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አካል በማድረግ የብልጽግና ጉዞን እዉን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል ።
የፓርቲ አደረጃጀት ይበልጥ ማጠናከር፣ የፓርቲ ፋይናንስ ማጠናከር፣ የአባላት መረጃ በዘመናዊ መንገድ ማደራጀት፣ የሰው ተኮር ስራዎች ላይ የመረዳዳትና የመደጋገፍ እና የመሳሰሉ ተግባራት የተሰሩ መሆናቸውን ከቀረበዉ ሪፖርቱ ማረጋገጥ ተችሏል ።
የብልጽግና ፓርቲ ኢንሼቲቭ የሆነውን፣ የኢትዮ ኮደርስ፣ ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎችንና ሌሎችን ተግባራዊ በማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ በሁሉም ህብረትና እና ቤተሰቦች ላይ ማስፋፋት እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል ።
የመንግስት እና የፓርቲውን ተግባራት በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን አደረጃጀቶችን መልሶ በማደራጀትና በማጠናከር በተቀናጀ መልክ ለመፈፀም ሀሳብ የመስጠትና የመታገል ስራ ከፓርቲ አባላትና አመራሮች እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ የድህረ ዘመን እውቀትን በመረዳት በእውነት ላይ በመመስረት የፓርቲው አመራር እና አባላት ስልታዊ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው በኮንፈረንሱ ተገልጿል።
የፓርቲውን አደረጃጀትና አሰራሮችን በመደበኛ ዕቅዳችን ጋር አጣጥሞ መስራት፣ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ የፓርቲውን ደንብና መመሪያን ተከትሎ መስራት፣ ህብረቶች በራሳቸዉ አሰራር ስርዓት ተግባራት የማከናወን ስራ በ2018 በጀት ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተመላክቷል።
በመጨረሻም በየህብረቱ በፓርቲ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቤተሰብ የእውቅናና የምስክር ወረቀት በመስጠትና የህብረት አመራሮች አደረጃጀት ሹመት በማጽደቅ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
