በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዕለት ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሲቪክ ማህበራት ፕሬዝዳንቶች በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በሰላማዊ፣ በህጋዊ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመሳተፍ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የአካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት መምህር አደም አሊ ፣የወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣት እሸቱ ብቃሙ እና የፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት በረከት ባሹ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብትና የሀገር ግንባታ መሠረት መሆኑን ጠቅሰዋል ።

በተለይም ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በያዙት ካርድ በንቃት በመሳተፍ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል እንዲጎለብት አስፈላጊ ሚና መወጣት እንዳባቸው አሳስበዋል ።

አመራሮቹ እንደገለጹት የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ሁሉ አቀፍ ተሳትፎን ያማከለ እንዲሆን ሁሉም ዜጎች ህግን በማክበር እና ለሀገራዊ አንድነትና ሰላም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የአካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝዳንቶች አካል ጉዳተኞች ከማንኛውም ዜጋ እኩል የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳላቸው በመገንዘብ፣ የምርጫ ካርድ የወሰዱ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ዕለት በነቃ ተሳትፎ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በምርጫው እለት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በምርጫ ቦርድ የተሰጠው መብት እንዲጠበቅ ማህበረሰቡ ለአካል ጉዳተኞች አጋዥና አካታች የሆነ ሁኔታ በመፍጠር የምርጫ ሂደቱን ያለምንም እንቅፋት እንዲሳተፉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተጨማሪም የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በምርጫ ቀን በተመደቡበት ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን በሰላም በጊዜ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በበረከት ኢዮብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *