ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሚመክረው 10ኛው የኦራን ሴሚናር ላይ እየተሳተፈች ነው

Spread the love

በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የተመራ ልዑክ በአልጄሪያ ኦራን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 10ኛው የአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ሴሚናር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ላይ የሚመክረው ሴሚናሩ ከአፍሪካ ህብረት በተሰጠው ሃላፊትነት መሰረት በአህጉሪቱ ሰላምና ጸጥታን በማረጋገጥ በኩል ባለፈው አስር ዓመት የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።

ዓመታዊ ሴሚናሩ በዋናነት በአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የጸጥታው ምክር ቤት የሚተላለፉ ውሳኔዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውጤታማ ሆነው እንዲተዋወቁና እንዲጠበቁ ማድረግ አላማው እንደሆነ ተመላክቷል።

በሴሚናሩ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ባደረጉት ንግግር ሴሚናሩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጦች ጋር በማጣመር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝም አምባሳደር ነብያት ማብራራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሲሚናር ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ የስርዓት ለውጥና፣ ሽብርተኝነትን ጨምሮ በበርካታ የአህጉሪቱ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *