የጥምቀት ከተራ በዓል በቦንጋ ከተማ በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

Spread the love

የጥምቀት ከተራ በዓል በየዓመቱ በተለያዩ ሀይማታዊ እና ባህላዊ ሥርዓቶች በደምቀት እንደሚከበር ይታወቃል ፡፡

የጥምቀት ከተራ በዓል ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ቦንጋን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

የጥምቀት በዓል በየዓመቱ ከጥር 11 ጀምሮ የሚከበረው ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ቅዱስ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባህር የተጠመቀበትን ዕለት ለማስታወስ ተፈልጎ እንደሆነ ይነገራል ፡፡

የጥምቀት በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ የተመዘገበ የኢትዮጵያ ትልቁ ቅርስ ነው ፡፡

የጥምቀት በዓል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ሲሆን በዓሉ የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት የሚያጠናክር ከመሆኑም ባለፈ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ በቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚሚ ከማሳደግ አንጻር ሚናው የጎላ ነው ፡፡

ይሄው የጥምቀት ከተራ በዓል በቦንጋና በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ዘገባው የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *