
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ ሲከናወን ቆይቷል። በዚህም የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ችግሮች የተለዩ ሲሆን ችግሮቹን ለመቅረፍም እየተሰራ ነው። ለአብነትም በዘንድሮው ዓመት ብቻ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የቀረበው የኃይል አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ከጥቂት ዓመት በፊት የአቅርቦት ጥያቄ የነበረበት የሲሚንቶ ምርትም አሁን ላይ ለውጭ ገበያ ጭምር ማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው። የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ 55 አዳዲስ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል።
