ዘላቂ የህዝብ ጥቅም እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ተደርጎ መስራት እንዳለበት ተገለጸ

Spread the love

የክልሉ የሱፐርቪዥን ቡድን በምዕራብ ኦሞ ዞን የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች የማጠቃለያ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

የድጋፍ እና ክትትል በመንግሥት እና በፓርቲው የተሰሩ ሥራዎች ጥንካሬዎች እና ጉድለቶች በማረም ለለውጥ መትጋት እንደሚገባ ተገልጸዋል።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የምክር ቤት አባል እና የክልሉ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደተናገሩት የድጋፍ እና ክትትል ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን ማዕከል በማድረግ የዛሬዉ ማጠቃለያ በመሆኑ በመዋቅሮቹ አበረታች ሥራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

በህብረተሰቡ ተሳትፎ በርካታ መንገዶች መገንባታቸው የህዝብ ንቅናቄ አበረታች መሆኑ የትምህርት ለትውልድ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ በርካታ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ ተናግሯል።

የኩታ ገጠም እርሻ ሥራዎች የተቀናጀ የተፋሰስ መደበኛ መስኖ ሥራዎች እየተሰራ ያሉት መታየቱ ጠቅሷል።

ከታዩ ሥራዎች መካከል በቤሮ ወረዳ ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጠው የጤና አገልግሎት ተቋማት ግንባታ በህብረተሰብ ተሳትፎ የቀዶ ጥገና ክፍል ግንባታ፤ የግሬደር ማሽን ግዢ ፍጽሞ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ እና የህዝብ መመላለሽያ መኪና ግዢ ፈጽሞ አገልግሎት ላይ በመሆኑ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብልዋል።

በማጂ ቱም ከተማ ያለው የንፁህ መጠጥ ዉሃ ሥራዎች በጋቺት ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎ በርካታ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ እና የመንገድ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ አስገንዝበዋል።

በጎሪ ጌሻ ወረዳ ፓርቲው በራሱ ተቋም የማድረግ ሥራዎች እና በቀበሌ ደረጃ የቢሮ ግንባታ በማድረጋቸው በተመሳሳይ በቤሮ ወረዳ ያሉት ሥራዎች አበረታች እና ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎች መሰራቱ ተናግሯል።

ዘላቂ ሠላም ለማምጣት እና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በአርብቶ አደር አካባቢ የታየው ያለው ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የህዝብ እና የመልካም አስተዳዳር ችግሮች የመፍታት እና ተጠቃሚነት ላይ ከወትሮው ትኩረት መደረግ እንደሚገባ ጠቅሷል።

በጤና ዘርፍ በተለይም የማጤመ አፈጻጸም ሥራዎች አጀንዳ እስከ ቀበሌ ድረስ እንዲወርድ መደረግ እና እየታየ ያለው መነቃቃት መጠናከር እንዳለበት ተናግሯል።

በሁሉም መዋቅሮች በርካታ ዉጤታማ ሥራዎች መሰራቱን ጠቅሶ ያሉት ጥንካሬዎች በማስቀጠል ጉድለቶችን የእቅድ አካል በማድረግ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

በተግባር ተኮር የሱፐርቪዥን ቡድን ሥራዎች የዞን አመራሮች በቀጣይ መሰረት የሚገባ የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ዉይይት መደረጉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *