
በሌማት ትሩፋት ስራዎች አስደናቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በተመለከተ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል።
በእንቁላል፣ በወተት፣ በስጋ ምርት ኢትዮጵያ ቀድማ የጀመረችው እንቅስቃሴ ትክክለኛ መሆኑ አሁን ላይ ያለው የአለም የገበያ ቀውስ ጥሩ አመላካች ሊሆን ይችላል ብለዋል።
የተሰራው ስራ በቂ ነው ብለን አናምንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እስካሁን በተከናወኑ ስራዎች አስደናቂ እመርታ መመዝገቡን ጠቁመዋል።
