የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ የሲቭል ሰርቪስ ሪፎርም በተቀመጠው አሠራር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የፋይናንስና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ለአመራርና ባለሙያዎች ስልጠና በቦንጋ እየሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊና ፊዝካል ፖሊሲና መንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ መለሠ ኡሮ የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ በሀገር ደረጃ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸዋል።

ለዚህም ስኬታማነት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመተግበር ላይ መሆኑን አንስተው፤ ትኩረት ከተሰጠባቸው ዘርፎች አንዱ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገር ደረጃ በተመረጡ ተቋማት የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም ስራዎች መጀመሩን በመግለጽ በክልል ደረጃ በተመረጡ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ዓላማውም በሀገር ደረጃ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖር ለማድረግ እያንዳንዱ ተቋም ብቃት ያለውን ፈጻሚ በማዘጋጀት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ የዜጎችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ለማስቻል እንደሆነ አቶ መለሰ አንስተዋል።

ስልጠናው በሀገራችን ያስመዘገበቻቸውን ድሎችን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም ምርትና አገልግሎትን በስፋትና በጥራት ለተገልጋዩ ለማቅረብ ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።

በመሆኑም ሪፎርሙ የሚጀርባቸው ተቋማትን ማብቃትና ጠንካራና ብቃት ያለውን ፈጻሚ ለማዘጋጀት፣ ጠንካራ አደረጃጀትና አሰራርን ለመዘርጋት ሰልጣኞች ስልጠናውን በተገቢው እንዲሳተፉ አሳስበዋል።

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ የስልጠና ሰነድ በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሆኑት በአቶ ሳምሶን መለሰ ለሰልጣኞች በመቅረብ ላይ ይገኛል።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *