የበልግ እና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ሚናቸውን በተገቢው መወጣት አለባቸው ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2018 ዓ.ም የበልግና ተፋሰስ ልማት ሥራዎች ክልላዊ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ የበልግ እና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በልዩ ትኩረት መምራት በመቻሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት እያሳየ ይገኛል።

የ2018 ዓ.ም የበልግ እና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በተደራጀ መልኩ እንዲከናወኑ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ሚናቸውን በተገቢው እንዲጫወቱ አስገንዝበዋል።

በዘንድሮ በልግ አዝመራ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አንድም የእርሻ መሬቶች ጾም ማደር የለበትም ሲሉ ነው ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ) ያሳሰቡት።

በዚህም መታረስ የሚችሉ በግል፣ በቡድና በኢንቨስትመንት ስም የተያዙ የእርሻ መሬቶችን በአግባቡ በማረስ በዘር መሸፈን ይጠበቃልም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

በከተሞች የሚገኙ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች እንዲለሙ ማድረግ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በእርሻው ዘርፍ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው አርሶ አደሩ በዘመናዊ ተክኖሎጂዎችን ተጠቅመዉ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ አለባቸው ነው ያሉት።

በዚህም ምርጥ ዘር ፣ አፈር ማዳበሪያና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን በተሟላ መልኩ መጠቀም እንደሚያስፈልግም ነው ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የተናገሩት።

ለበልግና ለተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ስኬታማነት በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችና እምቅ የልማት አቅሞችን በመጠቀም ህዝቡን በማስተባበር እንዲሁም አደረጃጀቶችን በማጠናከር ሊሰራ ይገባል ብለዋል ።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *