





በማጠቃለያ መርሃ -ግብር ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ እንደገለፁት ስልጠናው በአመራሩ ዘንድ የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የሚያስችልና ለቀጣይ ተልዕኮ ራሱን ለማዘጋጀት የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስልጠናው ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመፍጠርና የጋራ መግባባትና አረዳድ የፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አመራሩ በተሰማራበት መስክ ሁሉ አገልጋይና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመገንባትና ህልሞችን ወደ ተጨባጭ እውነታነት ለመቀየር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መስራት እንዳለበትም አክሏል።
ጠንካራና ዘላቂነቱ የሚያስተማምን የሀሳብና የተግባር አንድነትን መገንባት ቁልፍ የፓርቲያችን ተልዕኮና ተግባር አድርጎ በመውሰድ እና ግንዛቤን በማዳበር ለላቀ ውጤት መረባረብ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።
አመራሩ እንደ ሀገር ፣ክልልና ዞን የተገኙ ስኬቶችን በአግባቡ በመገንዘብና ፈተናዎችን በጽንኦት በማለፍ ተጨማሪ ስኬቶች ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
ህልሞችን ወደ ተጨባጭ እውነታዎች ለመቀየር የሚያስፈልገው የተስፋ ስንቅና ጉልበት ጨብጠው በሚመሩት ተቋማት እመርታዊ ውጤት ለማሰመዝገብ በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።
አመራሩ በትርክት እመርታ ፤ በፖለቲካ ፤ በምጣኔ ሀብት ፤ በፀጥታና ደህንነት ፤ በሥነ-ምግባራዊና ሰብዓዊ እመርታ ለማምጣት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ በውጤታማነት በመምራትና በማስፈጸም ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ብልጽግና ምዕራፍ ለማሻገር የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።
የምንሰራቸው ስራዎች በሙሉ የህዝቡን ቅቡልነትና እርካታን የሚያረጋግጡ መሆን መቻል አለባቸው ብለዋል።
በዞኑ በግብርና የሚታረስ መሬት፣ የዉኃ አማራጮች እና አምራች የሰዉ ኃይል አቀናጂቶ በመጠቀም በበጋ ስንዴ፣የሌማት ትሩፋት በፍራፍሬ፣በቅመማ ቅመምና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተግቶ በመስራት ሀብት በመፍጠር ኢኮኖሚያችን ማሳደግ መቻል እንደሚገባ በዕለቱ ማጠቃለያ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
ፓርቲያችን ብልጽግና የበጎነት እሴት ልዩ መገለጫው በመሆኑ የፓርቲያችንን ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ በመከተል ሰልጣኞቹ ለበጎ አድራጎት ተግባር የሚውል ከ1መቶ 25 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
በልጠናው ከዩኒቨርሲቲ ፣ ከክልል ተቋማት ፥ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ከ 598 በላይ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በስልጠናው የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ስልጠናው ተጠናቋል።
