




በመኸር የግብርና ስራዎች ከ126 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያም ጥቅም ላይ እንደሚውል ታውቋል።
አልቆ ማቀድ፣አልቆ መስራት ለምርታማነት ዕድገት! በሚል መሪ ቃል የግብርና መኸር ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል።
በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታትም በተሰሩ የግብርና ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል ሲሉም ተናግረዋል ።
በ2016/17 በመኸር የግብርና ስራዎች በዋና ዋና ሰብሎችና በሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ388 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በማልማት 15.7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል ።
በተከናወነው የመኸር ግብርና ስራዎች ከ90 ሺህ በላይ ሄክታር በክላስተር መልማቱንም ነው ያሰታወቁት።
በተከናወነው የበልግ ግብርና ስራዎች ከ394 ሺህ በላይ ሄክታር በዘር መሸፈኑንና ከዚህም ውስጥ ከ25 ሺህ በላይ ሄክታር በትራክተር እርሻ እንዲሁም ከ80 ሺህ በላይ ሄክታር በክላስተር መልማቱን ተናግረዋል ።
በመኸርና በበልግ የግብርና ልማት ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም ከ145 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉንም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።
በ2017/18 የመኸር ግብርና ስራዎች በዋና ዋና ሰብሎችና በሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ401 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማልማት 17.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ይሰራልም ብለዋል።
ይህንንም ውጤታማ ለማድረግ ከ126 ሺህ በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ እንደሚውልም ተናግረዋል ።
በመኸር የግብርና ስራዎች በክልሉ ከ48 ሚሊዮን በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማም ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል ።
በክልሉ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን እያሳየ መምጣቱን የጠቆሙት ሃላፊው በዚህ መኸር በዘርፉ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በክልሉ በ23 ወረዳዎች በ47 ቀበሌ በድጋፍ ክትትል የተለዩ 73 መንደሮች የሌማት ትሩፋት ቁመና እንዳኖራቸው በ90 ቀናት አፅንኦት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
በመኸር እርሻ ወቅት በራስ አቅም ችግሮችን የመቅረፍ ልምድ በማዳበር 1553 በላይ ሄክታር መሬት የማልማት ዕቅድ መያዙም ታውቋል
በተጀመረው የግብርና ንቅናቄ መድረክ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
የቴክኖሎጂ ስርፀት ፣የተሟላ የበለሙያ ምክረ ሃሳብ አለመጠቀም ፣የሌማትትሩፋት ግብኣት አቅርቦት ችግር እና መሰል ተግዳሮቶች እንዲቀረፉ በንቅናቄው ተሳታፊዎች እንዲመከርበትም ተጠይቋል
በክልሉ የመኸር ግብርና ስራዎች ንቅናቄ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የዞንና የወረዳ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።
በታጠቅ አበበ
