ሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መካሄድ ጀመረ

Spread the love

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን÷ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ፡፡

#FMC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *