የዋጋ ግሽፈቱ ወደ 14.4.% ዝቅ ብሏል:: ምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች ላይ ግሽፈቱ ወደ 12% ወርዷል፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Spread the love

በበጀት ዓመቱ የዋጋ ግሽፈት በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው 22% ወደ 14.4% መውረዱንና ከዚህ ውስጥ ምግብና ምክብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ግሽፈት ወደ 12% መውረዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ከብሔራዊ ባንክ ዓመቱን ሙሉ ብድር ሳይወሰድ ዓመቱን ማጠናቀቁ፣ በፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ ላይ የተወሰደው እርምጃ የዋጋ ግሽፈትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ከፍተኛ ድጎማ መደረጉ፣ በመላ ሀገሪቱ 1400 በላይ የቅዳሜ እሁድ ገበያ ተመቻችተው አምራቾችንና ሸማቾችን በቀጥታ ማገናኘት መቻሉ እና የገበያ ትስስር በመፍጠር የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በተሰራው ስራ ገበያን በማረጋጋት በኩል ትልቅ ውጤት እንዲመጣ ማስቻሉን አብራርተዋል፡፡

የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽፈትን ለመቀነስ ዋነኛው መፍትሔ ምርታማነትን ማሳደግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም የዋጋ ግሽፈቱ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ላይ ከፍትኛ ጫና እንዳያሳድር 350 ቢሊዮን ብር ድጎማ መደረጉን አንስተው የዋጋ ግሽፈትን ከፍላጎት ጋር ማማጣም የሚቻለው የእያንዳንዱን ሰው ገቢ ማሳደግ ሲቻል በመሆኑ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገትን ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነውም ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *