በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጸደቀዉ የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/ 2017 የጤና ባለሙያዎችን የረጅም ግዜ ጥያቄ የሚመልስ ነዉ።

Spread the love

በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጸደቀዉ የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/ 2017 ከጤና አገልግሎትና አስተዳደር ጋር ተያይዞ ከሀረብረተሰቡና ከጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ተገቢ የሆኑ ብዙ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ ትልቅ መሰረት የጣለና ብዙ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል ነዉ።

ከነዚህም ዉስጥ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ብቻ እንኳን ብናይ:-

1/ የጤና ዘርፍ ሰራተኛ መብት በሚደነግገዉ አንቀጽ ስር የጤና ዘርፍ ሰራተኛ በስራው ባህሪይ ምክንያት ተጋላጭ ለሚሆንባቸው በሽታዎች ቅድሚያ የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለዉ እና የጤናው ዘርፍ የመንግስት ሰራተኛ የጤና መድህን አባልነት ሙሉ መዋጮ በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን ይደነግጋል ። ዝርዝር አፈጻጸሙም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ እንደሚወሰን ተገልጿል።

2/ ከሕክምና አገልግሎት ጋር የተያየዙ ክሶች ስለሚቀርቡበትና ስለሚሰሙበት ሁኔታን በተመለከተ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠረ ማንኛውም የጤና ባለሙያ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት በቁጥጥር ስር የሚውለው ባለሙያዉ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ምክያታዊና አሳማኝ ጥርጣሬ እንዲኖር የሚያስችል ማስረጃ ሲኖር ብቻ መሆኑን ይደነግጋል። እንዲሁም ፍርድ ቤት በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ምክንያት በወንጀል ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት ባለሙያ ላይ ፍርድ ለመስጠት የጤና ሙያ ስነ-ምግባር ኮሚቴ ዉሳኔን እና ሌሎች ማስረጃዎችን በደምብ መመዘን እንዳለበት ያትታል።

ይህም ከዚህ በፊት በአንዳድ አከባቢ የህክምና ባለሙያዎች ለታካሚዎች የህክምና አገልግሎት እየሰጡ፣ ወላድ እናት እያዋለዱ፣የቀዶ ህክምና እና ሌሎቸ‍እ አገልግሎት እየሰጡ እያሉ ጭምር በቁጥጥር ስር የሚዉሉበትን ከማስቀረቱም በላይ ጤና ባለሙያዉ የሚሰጠዉን አገልግሎት በራስ መተማመን ተደራሽ እእንድያደርግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ይታመናል።

አዋጁ በፍጥነት ታትሞ እንድወጣ ከማድረግ ጎን ለጎን ከነዚህ እና ሌሎች ጋር ተያይዞ ለአፈጻፀም በአዋጁ ዉስጥ የተመላከቱ ደንቦችና መመሪያዎች በሚመለከተዉ አካል እየተዘጋጀ ይገኛል።

የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *