37 ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

Spread the love

በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ ባለፈው ዓመት አራት ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 300 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አንስተዋል።

መንግስት ለማዕድን ዘርፉ በሰጠው ትኩረት በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን የወርቅ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የማዕድን ሀብት ካላቸው ሀገራት ቀዳሚ ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *