“ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን አንፈልግም” ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፤ ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን እኛ አንፈልግም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ግን በጎረቤቶቿ መከበር አለበት ሲሉ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ እና የጎረቤቶቿ እሳቤ አንዳችን ለሌላችን በጣም አስፈላጊ መሆናችንን መገንዘብ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላም ካጣች ከተጎዳች ከኢትዮጵያ ያላነሰ የእኛ ጎረቤቶች ይጎዳሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቅና ከወዳጅ ጋር ያለው ሁኔታ በሚያዘልቅ መንገድ በጥንቃቄ አማካኝ ስፍራን ሳንለቅ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የሚያውካትን ተከላክላ መልማት እንደምትችል ጠቅሰው፤ የኤርትራ፣ የሱማሊያ፣ ሱዳን ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው ተባብረን ማደግ እንፈልጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አትበታተንም እራሷን ለመከላከል በቂ አቅም አላት፡፡ጠላቶች ነበሯት አሏት አይናቸው እያየ ግን እናንሰራራለን ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *