




“ትውልድ በመምህር ይቀረፃል፤ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል” በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የመምህራን ውይይት በቴፒ ከተማ እየተካሄ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት የትምህርት ስብራቶችን ለመጠገን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው የስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል፣ ማህበረሰቡ ለትምህርት ያለውን አመለካከትና ተሳትፎ በማሳደግ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል።
በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ የመሆን ህልማችንን እንደ ሀገር ለማሳካት የመምህራንና የትምህርት ዘርፉ ሚና ጉልህ እንደሆነ ገልፀዋል አቶ አለማየሁ።
የተጀመረውን የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የመምህራን ሚና የጎላ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ በትምህርት ሴክተሩ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመሻገር ትምህርት ቤቶች በቴክኖሎጂ የታገዙ ሊሆኑ እንደሚገባ አንስተዋል።
የሀገርቱን ማህበራዊና ፣ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን ከመጠገን አኳያ የመምህራን ሚና ቀላል እንዳልነበረ ያነሱት አቶ አለማየሁ መምህራን የሀገራችንን ችግር መፍቻ ቁልፍ ሀሳብ በማፍለቅ ጥልቅ ውይይት በማድረግ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን አለሙ በበኩላቸው እንደ ሀገር የትምህርት ሴክተሩን ሪፎርም ተከትሎ ከመጡ ለውጦች አንዱና ዋነኛው የትምህርት ቤቶችን ጀረጃ ማሻሻልና ጥራት ላይ በማተኮር የአስተሳሰብ ለውጥ መጥቷል ብለዋል።
ለውይይት መነሻ የሚሆን የመወያያ ሰነድ የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን አለሙ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በውይይት መድረኩ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ጨምሮ ከፍተኛ የዞን አመራሮች፣ ከሁሉም መዋቅር ከመንግስትና ከግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን እና የዘርፉ አመራሮች፣የመምህራን ማህበር ተወካዮች እየተሳተፉ መሆናቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
