




የሶርጋ ኢኮ ሎጅ ግንባታ ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሶርጋ ሐይቅ ላይ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ በአሁኑ ወቅት በ14 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ከነቀምቴ ከተማ በ6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብቻ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ መሆኑን አመላክተዋል።
ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመጥቀም በክልሉ ዘላቂ ቱሪዝምን የሚያበረታታ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
