





የቤንች ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ ቢስት ባር በሼይቤንች ወረዳ ዣዥ ቀበሌ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች መከበር ጀምሯል።
በዓሉ ለሁለት ቀናት በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች ተከብሮ የሚውል ሲሆን በዛሬው ዕለት አንዱ የቤንች ነገድ ሼቴት በሚገኙበት ዣዥ ቀበሌ የፌደራል ፣የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በባህላዊ አጨፋፈር በድምቀት ይከበራል።
በዓሉ በነገው ዕለት በሚዛን አማን ከተማ በአማን አየር ማረፊያ የፌደራል ፣የክልልና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የሚከበር ሲሆን በፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ሁነቱ ከስፍራው በቀጥታ የሚሰራጭ ይሆናል።
በታጠቅ አበበ
