
ህዝበ ሙስሊሙ ለኢትዮጵያ ሰላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ማሰብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ምዕመኑ በተለይ በረመዳን ወር ምስኪኖችን ከማገዝ ጎን ለጎን ስለ ሀገሩ ዘላቂ ሰላም ወደ ፈጣሪው እንዲጸልይም አሳስበዋል፡፡
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጀምሮ 4ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የጸጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
