ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው::

Spread the love

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ ግብር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት አማካሪና የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርኃ-ግብር የበላይ አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ በዚሁ ጊዜ፤ ረመዳን የመሰባሰቢያና የአብሮነት ወር ነው ብለዋል።

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አንድነትን የሚንጸባረቅበት፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት እንዲሁም አብሮነትን የበለጠ የሚጎላበት መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *