ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ውሎው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ::

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል ።

ምክርቤቱ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 5ኛ

መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች ቀርበዋል።

በዚህም መሠረት የተከበሩ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ የምክር ቤቱ የህግ ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ረቂቅ አዋጆችን ለምክርቤቱ አቅርበዋል።

1.የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የግብርና ስራ ገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ፣

2.የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣

3.የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈጻጸም ስነስርዓት ረቂቅ አዋጅ፣

4.የክልል የየእርከኑ ምክር ቤት ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 06/2014ን ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ምክርቤቱ የቀረቡለትን ረቂቅ አዋጆች ከመረመረ በኋላ ስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *