የሀገራችን ዜጎች በመረጡት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ የመሆን ህገ መንግስታዊ መብት እንዳላቸው ይታወቃል።
በመረጡት የሥራ ዘርፍ ውስጥ በመሰማራት ከሚያገኙት ገቢ ላይም እንደገቢ መጠናቸው ግብር የመክፈል ግዴታም ተጥሎባቸዋል።
መንግስት ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ያደረገው የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የግሉን ዘርፍ የሚያበረታታ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በክልላችን ሰፋፊ የሥራ መስኮች በመፈጠራቸው የዜጎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን የሚችሉባቸው በርካታ ዕድሎች ተፈጥረዋል፤ በዚህም ሂደት እንደ ሀገር ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ እየተቻለ መጥቷል።
ሀገራዊ ለውጥን ተከትሎ ተግባራዊ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲም በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ እያጋጠሙ ለነበሩ ችግሮች መሰረታዊ መፍትሄ እየሰጠ በመምጣቱም ምርትና ምርታማነት በስፋት እንዲጨምር ከማድረግ
ባሻገር የነበረውን ኢኮኖሚያዊ እድገት በተሻለ ሁኔታ በማስቀጠል የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ እንዲሆን መሰረት እየጣለ ይገኛል።
የክልሉ መንግስት ግብር የመሰብሰብ ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን መሰረት በማድረግ የግብር ስርዓቱ የሚመራባቸውን ህጎችን በማውጣትና የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ግብር በመሰብሰብ ለክልሉ ህዝቦች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና ለሌሎች መንግስታዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያነት እንደሚያውል ይታወቃል።
ለዚህም በክልሉ መንግስት የታቀዱ የመሠረተ ልማት፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ግቦችን ለማሳካት
የውስጥ ገቢ ማሳደግ ወሳኝ ነው፡፡
በክልሉ መንግሥት ለአስፈፃሚ አካላት በተሰጠው ስልጣን መሠረት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገቢ አቅምን በማሳደግ ወጪን በውስጥ ገቢ ለመሸፈን ግብ ጥሎ እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህም ከተመሠረተበት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም በከፍተኛ ደረጀ እያደገ መጥቷል፡፡
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በክልሉ የተጀመረው የልማት እንቅስቃሴ ለማፋጠን ተጨማሪ ገቢዎችን በአግባቡ ለመሰብሰብ እንዲያስችል ተጨማሪ የገቢ መሻሻያዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡
የክልሉ ወጪን በገቢ ለመሸፈን በከተሞች አካባቢ የመዘጋጃ ቤታዊ የምጣኔ ተመን መሻሻያ፣ የፊትህ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ምጣኔ፣ የተለያዩ የልኳንዳ ቤቶች ዋጋ ተመን፣ የጫት ቀረጥ እና የገጠር መሬት መጠቀሚያ ገቢ ግብር ተመንን በማሻሻልና በክልሉ ተግባራዊ በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ክልሉ አርንጓዴ ነው ያሉት ወ/ሮ ህይወት በአርንጓዴነቱ ቡናና የተለያዩ ለኤክስፖርት የሚሆኑ ምርቶች የሚመረትበት በመሆኑ ይህም ክልሉን ለኢንቨስትመንት ሚቹ እንደሚያደረግም ተናግረዋል፡፡
ይህንን ለኢንቨስትመንት ሚቹ የሆነውን መሬት በአግባቡ እየተጠቀመን ባለመሆኑ በዚህም መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን የጠቀሱት ኃላፊዋ ከዚህ ቀደም ሲል ከኢንቨስትመንት መሬቶች ይገኝ የነበረው የ2.4 ሚልዮን ገቢን በ2016 በጀት ዓመት ወደ 72 ሚሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ ወደ አንድ ሚሊየን ሄክታር የሚሆን የሚታረስ የገጠር መሬት መኖሩን ያነሱት ወይዘሮ ህይወት የገጠር መሬት መጠቀሚያ ገቢ ግብር ተመን ላለፉት ሃያ ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው በመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ከዚህ ዘርፍ መግኘት አልተቻለም ነበር ብለዋል፡፡
ለዚህም መጠነኛ የሆነ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ገቢ ግብር ተመን ማሻሻያ ከተደረገ ወዲህ ክልሉ ሲመሰረት በ2014 በጀት ዓ.ም 11 ሚሊዮን ሲገኝ የነበረውን የገጠር መሬት መጠቀሚያ ገቢን በተያዘው በጀት ዓመት ወደ 98 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልሉ ምክርቤት ጉባኤ የገጠር መሬት መጠቀሚያ አዋጅ ቀርቦ የጸደቀ ሲሆን በቀጣይም አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሲል ግብርናው አጠቃላይ ለክልሉ 2 ከመቶ ገቢ ድርሻ ብቻ ያለውን ወደ 12 ከመቶ ከፍ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት ወ/ሮ ህይወት፡፡
ገቢ መሰብሰብ ለህብረተሰቡ ልማት የሚውል ነው ያሉት ኃላፊዋ ለዚህም በክልሉ እየተደረጉ ያሉ የገቢ ማሻሻያዎችም በክልሉ ገቢ ላይ ከፍተኛ መሻሻሎችንና ለውጦችን እያመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከግብር አስተዳደር አዋጅ አንፃር የዕለት ገቢ ግመታ በየሶስት ዓመት መደረግ እንደሚገባ የሚደነግግ ቢሆንም ላለፉት ስድስት አመታት የዕለት ገቢ ግመታ ሳይደረግ በመቆየቱ ምክንያት ከዘርፉ የሚፈለገውን ገቢ ማግኘት እንዳልታቸለ የገለፁት
ወ/ሮ ህይወት፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ጥናቶችን በማድረግ በክልሉ በሚገኙ 45 ሺህ (ሐ) ግብር ከፋዮች ዕለት ገቢ ግመታ ተመን በማድረግ በዚህም ዘርፍ ከዚህ ቀደም ይሰበሰብ ከነበረው 142 ሚሊዮን ገቢ በ2016 በጀት ዓመት 394 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሰራ እንሆነም ጠቅሰዋል፡፡
በክልሉ የደረጃ ሐ የግብር ወሳኔዎች ከብልሹ አሰራር እና ከሌብነት በፀዳ መልኩ እንዲሰራ እና ለግብር ከፋዮች ተደራሽ ለማድረግ ሲስተም በማዘጋጀት ተግባራዊ በማድረግ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት ኃላፊዋ በዚህም የተሻለ አፈፃፀም እና ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡
ደረሰኝ የመቀበል ምጣኔ ከተጠቃሚው ማህበረሰብ አንፃር በቂ ነው ባይባልም ከበፊቱ እየተሻሻለ መጥቷል ያሉት ወ/ሮ ህይወት የክልሉ ገቢዎች ቢሮም በክልሉ ከሚከናወኑ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ተገቢውን ግብር በመሰብሰብ በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ዕቅዶች ማስፈፀሚያነት የሚሆን የፋይናንስ ወረት
ለመሰብሰብ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል።
ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት ከ6.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የክልሉን መንግሰት ወጪ 48.5 በመቶ ለመሸፈን ግብ ተይዞ ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ከወትሮው በተሻለ መልኩ በማሻሻል በግማሽ አመቱ 2 ቢሊዮን 721 ሚሊዮን 466 ሺህ 156 ብር ከ45 መሰብሰቡን ወ/ሮ ህይወት ገልጸዋል ፡፡
ይህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 717 ሚሊዮን 882 ሺህ 710.48 ብልጫ እንዳለው ጠቅሰው የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ እንዲጠናከር መላው የክልሉ ህዝብ የበኩልን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
ወ/ሮ ህይወት አክለው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ለተሰበሰበው ገቢ በየደረጃው ያለው አመራር የገቢ ተቋምን መደገፋና የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችና ተመኖች መሻሻላቸው ለአፈፃፀሙ አጋዥ እንደነበር ገልፀዋል።
ባለድርሻ አካላትን በተገቢው መንገድ የድርሻቸውን የማይተካ ሚና እንዲወጡ በማስቻል የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ኃላፊዋ ከግብር ህግ ተገዥነት አንፃር በተቋሙ 10 ሰራተኞች ከክልል ማዕከል ጀምሮ ከዲስፒሊን ጀምሮ በወንጀል ከ6 እስከ 10 ዓመት ፍርድ እንዲቀጡ ሲደረግ በተሳሳተ የሂሳብ መመዝገቢያ ማሽን ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ በወንጀል ተከሶ በ10 ዓመት እስር መቀጣቱን አብራርተዋል።
በግብይት ወቅት ደረሠኝ የመስጠትና ጠይቆ ያለመውሰድ ችግር ለዕቅዱ ስኬት ፈታኝ ነበር ያሉት ኃላፊዋ ሸማቹ ማኅበረሰብ በግብይት ወቅት ደሰሠኝ ጠይቆ በመውሰድ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የተጣለበትን ዕቅድ አሟጦ ለማሳካት በማስተማር የታክስ ንቃተ ህሊና ስራን ከማጎልበት ጎን ለጎን የታክስ ህግ ተገዥነት ስራ በተለየ ትኩረት ይሰራል ብለዋል ወ/ሮ ህይወት።

Very nice progress
you are welcome. keep in touch!