በልዑኩ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ይገኙበታል።
የሥራ ኃላፊዎቹ ታርጫ ከተማ ሲደርሱ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑካኑ በዳውሮ ዞን በሚኖራቸው ቆይታ በቀጣዮቹ ቀናት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኙና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን እንደሚያስመርቁ ይጠበቃል።