ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የታርጫ ከተማ ንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ።

Spread the love

ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ውጪ የተገነባው የታርጫ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተኙበት ተመርቋል።

ከተለያዩ ረጂ ተቋማት በተገኘው 170 ሚሊዮን ብር እና 1.142 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገነባው የውሃ ፕሮጀክት ከ96 ሺህ በላይ የከተማውን ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ከሁለት የከረሰ ምድር የውሃ ምንጮች በሚገኝ ውሃን በከተማው በሶስት ቦታ በተዘጋጀው ማጠራቀሚያ በማከም በቀን 700-800 ሜትር ክዩብ ወሃ እያመረተ ለከተማው ህዝብ እንደሚያቀርብ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ 10 የውሃ ቦኖ፣ 12 ኪሎሜትር የሚጠጋ ዋና መስመር ዝርጋታ እንዲሁም በከተማው ሶስት የተለያዩ ቦታዎች የሳንቴሽን አግልግሎት ማዕከላት የያዘ ነው።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *