


ኢትዮጵያ “ደህንነቱ ለተጠበቀ ነገ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል ትብብር” በሚል መሪ ሀሳብ በዱባይ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የፖሊስ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው።
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራው ልዑክ በፈረንጆቹ ከመጋቢት 5 እስከ 7 ቀን 2024 በዱባይ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ልዑካን ቡድኑ በቦታው ሲደርስ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንሰላ ጀነራል ፅ/ቤትና በአቡዳቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ አቀባበል ተደርጎለታል።
ኮሚሽነር ጀነራሉ ከዱባይ ፖሊስ ዋና አዛዥ ሌተና ጀነራል አብዱላህ ከሊፋ አል ማሪ ጋር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጎንዮሽ ውይይት አድርገዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
