በበርሊን ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀመረ::

Spread the love

በጀርመን በርሊን በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) ጀምሯል።

ይህ ኤግዚቢሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ካምፓኒዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው።

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው፤ ኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነቻቸው ያሉ የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦችን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነች ያለችውን የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦች እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ሚኒስትሯ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋርም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል።

በዚህ ኤግዚብሽን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *