ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ




የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና ካቢኔ አካላት ጋር በክልሉ የትምህርት ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል ።
በውይይት መድረኩ በክልሉ በቀጣይ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል እና ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ በሰፊው ምክክር ተደርጓል።
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የክልሉን የትምህርት ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ያለውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ከትምህርት ስርዓት ጋር አስተሳስሮ መምራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
በየጊዜው ትምህርት ስራ ያለበትን ሁኔታ እየገመገሙ ቀጣይ አቅጣጫ እያስቀመጡ መሄድ ተገቢ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ስራ ተማሪዎችን ማስተማር ብቻ ሳይሆን ለተማሪዎች በቂ እውቀትና ክህሎት በማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልፀው ለዚህም ትምህርትን ከፖለቲካ ነፃ አድርጎ መምራት ይጠይቃልም ብለዋል፡፡
በክልሉ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ሚንስቴር መስሪያ ቤት 3 መኪና እና 48 ሞተር ሳይክሎችን ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡
ትምህርት ለትውልድ ትምህርት ቤቶችን ደረጀ ለመሻሻል አኳያ በክልሉ የተሰራው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ህብረተሰቡን በማስተባበር ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ በክልሉ የትምህርት ስርዓት ለማሻሻል እና ለማጠናከርና በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርቷል።
ይህንን ለማስጠበቅ የክልሉ መንግስት በመምህራን ልማት፣ መሠረተ ልማት፣ የመመሪያው ቁሳቁስ የማሟላት እና በአርብቶ አደር አካባቢ የተማሪዎች ምገባ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ሰፊ ስራ እየሰራ እንዳለ ገልፀዋል ።
በአሁኑ ሰዓት ዝቅተኛ የተማሪ ውጤት የተመዘገበውን በመቀየር የተሻለ የትምህርት ስርዓት ለመገንባት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር ላይ በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም አመልክቷል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በክልሉ ያሉ 90% የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከሚፈለገው ደረጀ በታች መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ለመቅረፍ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን እውን በማድረግ ትምህርት ቤቶችን ደረጀ ለማሻሻል ሳፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ለዚህም ከ261 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡንና የትምህርት ስራን ውጤታማ ለማድረግ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ክልሉ በማምጣት የትምህርት ዘርፉን ለመቀየር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በውይይቱ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።
በተከተል ወ/ሚካኤል
