በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከያ እና ለመቆጣጠር የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መስራት እንሚጠበቅ ተጠቆመ::

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት የሲ.ዲ.ሲ ፕሮጀክት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በክልሉ ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ባለፉት 6 ወራት ኤች አይ ቪ ኤድስ ከመከላከያ እና ከመቆጣጠር አንፃር በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረው በዚህ የተመዘገበውን ውጤት ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከያ እና ለመቆጣጠር የጤና ተቋማት የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መስራት እንሚጠበቅባቸው የጠቆሙት ኃላፊው ለዚህም በትምህርት ቤት፣ በሐይማኖት ተቋማት እና በተለያዩ ህዝባዊ አደረጃጀቶች ላይ በሚፈለገው መጠን ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *