ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በተለያዩ ፕሮግራሞች በቦንጋ ከተማ ተከብሯል::

Spread the love

ማርች 8 ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ133ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ በክልላችን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሃግብሮች ተከብሯል።

ዕለቱን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሴቶች ሊግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1990ዎቹ ተንሰራፍቶ የነበረው ግፍ፣ጭቆናና በደል በሴቶች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ንቅናቄ እንዲያደርጉ መንስኤ መሆኑን ተናግረዋል ።

በዚህም ከ15 ሺህ የማያንሱ ሴቶች ዝቅተኛ የስራ ሰዓት፣የተሻለ ክፍያእና የመምረጥና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለመጠየቅ በኒውዮርክ ከተማ ሰል እንደወጡም ወ/ሮ ውባለም ተናግረዋል ።

በክልሉ በዓሉ ሴቶችን እናብቃ፣ሰላምን እናስፍን፣ልማትን እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃግብሮች መከበራቸውን የተናግሩት ኃላፊዋ በክልሉ ከዚህ ቀደም ብሎ በሁሉም ዞኖች ለችግር ተጋላጭ እና ተጎጂ የሆኑ ሴቶችና ህጻናትን በመደገፍየማህጸን በር ጫፍ ቅድመ ምርመራና የደም ልገሳ በማድረግ በዓሉ መከበሩን አስታውሰዋል ።

በክልሉ የሚገኙ ሴቶች በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኙ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ውባለም በተቋማት የሚገኙ ሴት አመራሮችና በከፍተኛ የስራ መደቦች ላይ የሚገኙ ቡድን መሪዎች እርስ በርስ መደጋገፍ ፣በሴትነት የሚደርሱ በደሎችና ጫናዎች አንዳችን ለአንዳችን ተገን በመሆን ከስራችን ያሉትን በመደገፍና በማብቃት መትጋት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

በዚሁ ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በክልል ተቋማትና በሌሎች ተቋማት የሚሰሩ ሴቶች አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከትም ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ተሳታፊዎች በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ የሚተዳደሩና በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶችን ማብቃትና መደገፍ ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አንስተዋል ።

በዕለቱም ለአቅመ ደጋሞች የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፎችን በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *