ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችና ወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ሴቶችና ወጣቶች ገለጹ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ ”ከቃል ወደ ባህል “በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ፓርቲው የክልሉ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የክልል መደራጀት ጥያቄውን ከመመለስ ባሻገር በክልሉ ትላልቅ ሀገራዊ እና ክልላዊ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ለመፈጸም በገባው ቃል መሠረት እየሰራና እየፈጸመ ይገኛል ነው ያሉት።

በዚህም በክልሉ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ እንዲሁም ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ከመፈፀም አንፃር አበርታች ወጤቶችን እየተመዘገቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካ ዘርፎች የወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ሴቶችና ወጣቶችን በፖለቲካ ተሳትፎ በውሳኔ ሰጪነት ወደፊት እንዲወጡ ከማድረግ አኳያ የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

ፓርቲው የያዛቸው ዕቅዶች፣ሀሳቦችና ህልሞች እንዲፈጸሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ያብራሩት አስተያየት ሰጪዎች በተለይም ፓርቲው በስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሴቶችና ወጣቶች እኩል ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት፣ በመሠረተ ልማት፣ በትምህርት እና በኑሮ ውድነት ላይ የጀመራቸዉን ሥራዎች አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከመፍታት አንፃርም በክልሉ ከፓርቲው ምስረታ በፊት የነበሩ የሠላም መደፍረስ ህብረተሰቡን በማወያየት በተሰራው ስራ አሁን ላይ በክልሉ አንፃራዊ ሠላም መስፈን የተቻለ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም በአስተያየታቸው ጠቁመዋል ፡፡

ብልፅግና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አካቶ በመስራት በርካታ የክልላችን የድሃ ድሃ እና አቅመ ደካማ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ብለዋል፡፡

በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በሁሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አመልክተዋል ፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል እና ፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *