



‹‹ከቃል ወደ ባህል›› በሚል መሪ ሀሳብ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ ህዝቦች ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 2ኛ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ ኮንፍረንስ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው ፡፡
በኮንፈረንሱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ የለውጥ ሂደቶችን አልፋ አሁን ላይ ለደረሰችበት ሁለንተናዊ ለውጥ የብልጽግና ፓርቲ ትናት፣ዛሬንና ነገን ያስተሳሰረ የፖለቲካ አውድ መሰረት አድርጎ በመስራቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የመደመር አስተሳሰብ የጎለበተበት ግዙፍ ፓርቲ መገንባቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለህዝቡ ቃል የተገቡ ተግባራት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች መከናወናቸውንም እንዲሁ አብራርተዋል ፡፡
በሀገራችን ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑ ስራዎች ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም የሚፈጥሩ የተለያዩ ሀገር በቀል ፕሮጀክቶች ተከናውነዋል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡
በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በተለይም በትምህርት በጤናና ማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት በዘርጋት ተጨባጭ ለውጦች በክልሉ መመዝገባቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡
ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በትምህርት ዘርፍ ሉብንን ችግሮች ለመቅረፍ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ማከናወን ተችሏል ብለዋል ፡፡
በጤናውም ዘርፍ ከቀድሞ ደቡብ ክልል 64 የጤና ፕሮጀክቶችን በመረከብ 18ቱን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ ተደርጓልም ብለዋል ፡፡
በመሰረተ ልማት ስራዎችም ባለፉት 3 ዓመታት ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የገጠር ቀበሌ መንገዶችና ድልድዮች መሰራታቸውን በንግግራቸው ገልጸዋል ፡፡
የክልሉን ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግም ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገንና ባለፉት 3 ዓመታት በተሰሩት ስራዎች የክልሉን የውሃ ሽፋን ወደ 43..7 ማድረስ ተችሏል ብለዋል ፡፡
ክልላዊ የግብርና ስራዎች የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስፋት እየተሰራበት እንደሚገኝ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያዩ የግብርና ስራ ኢኒሼቲቮች ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል ፡፡
በበጋ መስኖ ስንዴ ፣ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፣ በሌማት ትሩፋት ስራዎች በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል ፡፡ እነዚህን ወጥነት ባለውና በተቀናጀ መንገድ ትኩረት ተሰጥቶት በቀጣይ ይሰራበታል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡
ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠርና ተቃሚ ከማድረግ አኳያ ባለፉት 3 ዓመታት 171 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው አብራርተዋል ፡፡
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ባስተላለፉት መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ በህዝብ ገፊነት በድርጅት ሳቢነት ተጸንሶ ፈታን የሆነውን የለውት ጉዞዎችን ተጉዞ አኩሪ ውጤት እያስመዘገበ የሚገን ነው ብለዋል ፡፡
ፓርቲው በሰራቸው አኩሪ ተግባራት በፖለቲካው፣ በማህበራዊ፣በኢኮኖሚውና በዲፕሎማሲው ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ያስቻለ መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡
በዚህም በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ፍጥነትና ፈጠራን በመከተል በሀገራችን እየተመዘገቡ ላሉ ሁለንተናዊ ለውጦች የላቀ ደረጃ ላይ መድረስ ችላል ሲሉም አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል ፡፡
በፓርቲው 1ኛ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት በሀገራችን ትላልቅ ፕሮጀክቶች መፈጸማቸው ማሳያም መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በክልሉ በመላው አባላት ደረጃ የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነት ለማስረጽ በየደረጃው የአመራርና አባላት ማጥራት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል ፡፡
በቀጣይ ጊዜያት በፓርቲው የሚነደፉና በክልሉ መንግስት የሚዘጋጁ የመልማት ዕቅዶች ውጤታማ እንዲሆኑም መላው አባላችን በላቀ ቁርጠኝነት ለመፈጸም ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል ሲሉም አቶ ፍቅሬ አማን አሳስበዋል ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 2ኛው መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተመከሉ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነዉ ፡፡
በታጠቅ አበበ
