የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ Delivery and Distribution of Paramedic-Midwifery Stations በአገራችን ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት Herroes Foundation እና Pan African Public Private Partinership Development Center ከተባሉ ሁለት የሩሲያ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት እ.ኤ.አ. ማርች 20 ቀን 2024 በኤምባሲው ጽ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡
የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ቻም ኡጋላ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር በዛሬው እለት የተፈረመው የሶስትዮሽ ስምምነት የሁለቱን ወዳጅ አገራት ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ እንደሚያሸጋግረውና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድገው ጠቅሰው ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን በማሳሰብ በሚሲዮኑ በኩል ተገቢውን ድጋፍና ትብብር እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
ተፈራራሚ ወገኖች በበኩላቸው ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ሚሲዮኑን ጨምሮ ስምምነቱ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ፣ የ Herroes Foundation ዋና ስራ አስፈጻሚ Kirill Masliev እና የ Pan African Public Private Partinership Development Center ዋና ስራ አስፈጻሚ Oksana Mayorova ናቸው፡፡
