
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ከፊታችን ጥር 30/2016 እስከ የካቲት 1/2016 ዓ/ም በታርጫ ከተማ እንደሚካሄድ አስታወቀ።
ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለጉባኤው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ።
በዚህም ለጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ መተላለፉን አፈጉባዔ ወንድሙ ኩርታ አስረድተዋል ።
በጉባኤ የአስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመትየ6 ወር የስራ አፈጻጸም ቀርቦ በጉባኤው አባላት እንደሚገመገም ጠቅሰዋል ።
በጉባኤው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሌሎች አጀንዳዎች ቀርበው እንደሚጸድቁ አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ ገልጸዋል።
በታጠቅ አበበ
