የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና የጋምቤላ ክልሎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ተወያዩ

Spread the love

የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ በሁለቱ ክልል የሚገኙ አዋሳኝ ዞኖችና ወረዳዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች በጋራ በውይይትና በምክክር በመፍታት ቀጠናው የተረጋጋና የልማት አካባቢ ለማድረግ የታሰበ ነው ::

ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀጠናው አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የግድያና ዝርፊያ ችግር ጥቅት ፀረ ሰላም ሃይሎችና ሽፍቶች የሚፈጥሩት ችግር እንደሆነና ሰፊውን ህዝብ እንደማይወክል ታውቆ ሰላማዊና አጥፊ ሰዎችን በመለየት ችግር ፈጣሪዎችን ብቻ ተከታትሎ ለህግ በማቅረብ የህግ ማስከበር ስራ በመስራት ቀጠናው የተረጋጋና ሰላማዊ ለማድረግ ከህዝባቸው ጋር ተባብሮ እንደሚሠሩም በውይይቱ የተሳተፉ የሁለቱ ክልል አመራሮች ተናግረዋል ::

በሌላ በኩል በቀጠናው በወሰን የሚገናኙት ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ ዕቅድ በማውጣት በቀጠናው የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በመቅረፍ አካባቢው የሰላምና የልማት ቀጠና ለማድረግ እንደሚሠሩና በተለይም በሁለቱ ክልሎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና በጋምቤላ ህዝቦች መካከል ያለውን የልማት ትስስር ለማጎልበት እና ወንድማማችነትን ለማጠናከር የተጀመሩት ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል ::

በትናንትናዉ ዕለት በዲማ ከተማ በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የሁለቱ ክልል የሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች ፣ ከአኙዋ ብሔረሰብ ዞን፣ ከቤንች ሸኮ ዞንና ከምዕራብ ኦሞ ዞን የሚመለከታቸው የፀጥታ ስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የዲማ ወረዳ ፣ የቤሮ ወረዳ ፣ የሱሪ ወረዳና የጉራፈርዳ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *