



በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር በዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን የኮንታ ዞን የጉብኝት ቆይታ የገንጂ ኢሞታ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመጎብኘት ጀምሯል።
ልዑካኑ በትላንትናው ዕለት የዞኑን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ሪፖርት አዳምጦ ግብረ-መልስ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ሃሳብ አመንጪነት የተገነባውን የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅና የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮይሻ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ እና ሌሎችንም ልማቶች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
