ብልጽግና ፓርቲ በሀገራዊ ምርጫ ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገለፀ::

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን “ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የብልፅግና ፓርቲ የአባላት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተጠናቋል።

የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት ፓርቲያችን በሁለት ዓመት ተኩል ጉዞ ውስጥ የፓርቲ እሳቤ፣ አደረጃጀት እና አባትን አስተሳስሮ በመምራት “ቃል በተግባር” የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ውጤት የቀየረ ነው ብለዋል ።

ኮንፍራንሱ ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜያት ዉስጥ የተመዘገቡ የፓርቲዉ ስኬቶችን በማጎልበትና ጉድለቶችን ፈጥኖ በማረም ተነሳሽነት ፈጥሮ ለቀጣይ ተልዕኮ ስኬት በአባላቱ መካከል መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አቶ በድሉ ገልፀዋል።

ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ አመርቂ ድሎችን በወጉ በመያዝ የሚታዩ ጉድለቶችን በማረም የበለጠ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ጠንካራ ትግል እንደሚያስፈልግ ያነሱት አቶ በድሉ የፓርቲያችንን ቅቡልነት ለማረጋገጥ አባሉ የሚጠበቀውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

በመጨረሻም የብልጽግና ፓርቲ አባላት በባለፉት ሁለት አመት ከግማሽ ለሰራቸዉ ውጤታማ ሥራዎችን ተጋግዘውና ተደጋግፈው ለማስቀጠል እና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ባለ 7 ነጥብ የአቋም መገለጫዎች በማዉጣት ኮንፈረንሱ ተጠናቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *