ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል!

Spread the love

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ከደቂቃዎች በፊት ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 17 ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቂቃዎች በፊት በተጀመረው የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ በመገኘት፤ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ምክር ቤቱ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *