የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ መካሄድ ጀመረ!

Spread the love

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀመረ

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) መልስ እና ማብራሪያ ሊሰጡባቸው ይገባሉ የሚሏቸውን ጥያቄዎች እያነሱ ይገኛሉ።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28/2016 ለሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አባቶች ተወካዮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *