ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ቢሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ነው፡፡
• በአማራ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
• አለመግባባቶች ወደ ግጭት ከመግባታቸው በፊት የመንግሥት ዝግጁነት እንዴት ይገለጻል?
• የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመመከት ረገድ ምን እየተሠራ ነው?
• የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና አዳዲስ በመጀመር የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ በመንግሥት በኩል ምን እየተሠራ ነው?
• እንደ ሀገር ካለው የባሕር ወደብ ፍላጎት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ብዥታዎች ስላሉ ግልጽ ለማድረግ ያህል ማብራሪያ ቢሰጥ፣
• በአጠቃላይ ፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር በተለይም አንዳንድ ለብልሹ አሠራር የሚያጋለጡ ዘርፎችን ከሌብነት በጸዳ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደመንግሥት ያለው ቁርጠኝነት ቢገለጽ፣
• ለሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ስኬት የመንግሥት ድጋፍ ቢጠቀስ፣
• የፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጻም በምን ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው የሚሉና ሌሎች ማብራሪያና ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎች የምክር ቤቱ አባላት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
