ከምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች‼️

Spread the love

በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች‼️

የትግራይ ህዝብ ህጋዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተሰራ ያሉ ስራዎችስ ምንድናቸው፣

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ምን ታስቦዋል የመምህራንን አቅም ከመገንባትና የተርምህርት ቁሳቁስን ከማሟላት አንፃርስ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያላለፉ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ ምንድነዉ የሚሉት ይገኙበታል።

ሀላፊነት የጎደላቸው ሚዲያዎች የሚያሰራጩት መረጃ እያስከተለው ያለውን ሀገራዊ ጉዳትን ለማስቀረት ምን እየተሰራ ነው። የመንግስት ህግ የማስከበር ቁርጠኝነት ምን ይመስላል።

አንዳንድ የታጠቁ ሀይሎች ከጅምሩ እየተሳተፉ አይደለም የሚል ሃሳብ ይነሳል፡፡ አገራዊ ምክክሩ ሁሉን አሳታፊ እንዲሆን የመንግስት እገዛ እስክምን ድረስ ነው።

የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ መንግስት እንዳይኖር የተዛባ ትርክት ዋናው መንስኤ ነው፡፡ የተዛባ ትርክትን አስተካክሎ ችግሩን ለመሻገር መንግስት ምን አስቧል። የተዛባውን ትርክት ለማስተካከል ከሚረዱ መንገዶች ብሔራዊነት አንዱ ነው፡፡ ለመሆኑ ምን ማለት ነው የተዛቡ ትርክቶችን ለማስተካከል ያስችላል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሆና መመረጧ የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ጥቅሞች ቢገለጽ፤

የኑሮ ውድነትን የዋጋ ግሽበትን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፤ የተጭበረበሩ ሰነዶችና የትምህርት ማስረጃን ለማስቀረት በዘላቂነት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ የተረጋጋ የሀገረ መንግስትን ለመፍጠር መንግስት ምን እየሰራ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀርቡላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *