“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” ዓውደ-ርዕይ ነገ በይፋ ይከፈታል
“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል የሚካሄደው የዲፕሎማሲ ሣምንት ዓውደ-ርዕይ በነገው ዕለት በይፋ እንደሚከፈት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ዓውደ ርዕዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር የሁሉም ሕብረተሰብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። አምባሳደር መለስ (ዶ/ር)÷ “ዲፕሎማሲያችን ከአፍሪካ መዲናነት እስከ ዓለም ዓቀፍ መድረክነት” በሚል ሥያሜ በሚካሄደው ዓውደ-ርዕይ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ…
