የባህር በር ባለቤትነት ጠቀሜታ በምሁራን እይታ!

የባህር በር ባለቤት መሆን ለአንድ  ሀገር ያለው ጠቀሜታ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ኢኮኖሚን በማሳለጥ እና በሀገራት እና በህዝቦች መካከል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብርን በማጠናከር በኩል ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው፡፡ የባህር በር ባለቤት መሆን የሀገሪቱን ደህንነት ከማስጠበቅ ረገድ ጥቅሙ እጅግ ብዙ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት የባህር በር የነበራት ሀገር በአንድ በታሪክ…

Read More

የግብርናን ዘርፍ ለማዘመን ሜካናይዜሽን ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡ በዋናነትም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትና ኢኮኖሚ ለማሻሻል ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡ 

አደጉ የሚባሉት ሀገራት የግብርና ዘርፉን  ያዘመኑት ለሜካናይዜሽን ግብርና ትኩረት በማድረግ ትራክተር እና የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ ሆነዋል፡፡ ስለሆነም የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ያለ ትራክተር እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ፈጽሞ የማይቻል ጉዳይ ነው። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠፊና ለእርሻ አመቺ መሬት ያለ በመሆኑ ይህን መካናይዝድ በሆነ መንገድ በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ከክልሉ አልፎ ሀገሪቱን መመገብ የሚያስችል…

Read More

ደን ጠብቆ ያቆየዉን ህዝብ የሃብቱ ተቋዳሽ ለማድረግ ምን እየተሰራ ነዉ?

ሪፖርታዥ ደን ለሰው ልጆች ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። በተለይ የአየር ፀባይ ሚዛንን ከመጠበቅ አንጻር የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። በኢንዱስትሪ ማዕበል የተጥለቀለቁ የዓለም ሀገራት ከፍተኛ የተቃጠለ አየር ለተቀረው ዓለም ከማስረከብ ያለፈ ንጹህ አየር ማምረት ላይ ጠብ ያለ ተግባር አሳይተዋል ማለት ግን አይቻልም። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ሰፊ የደን ሽፋን ያላት ሀገር ቢትሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ የደን ሽፋን ምጣኔ…

Read More

የክልሉ አስፈፃሚ ተቋማት የዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የተግባር አፈጻጸም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ነዉ። በበጀት ዓመቱ ታቅዶ ወደ ተግባር በተገቡና ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ አንኳር ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል። የክልሉን ህዝቦች የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታትና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰሩ ዋና ተግባራት…

Read More

ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል ነዉ – አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የሴክተር አፈጻጸም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየገመገመ ነው፡፡ ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በወቅቱ፥ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የሁሉም ዘርፎች ደም ስር በመሆኑ በጋራ ልንሠራ ይገባል ነው ያሉት። በዚህም ባለፉት ጊዜያት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሳኩ ተግባራት መፈጸማቸውን…

Read More

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት አቶ ዳዊት ገበየሁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ።

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ሥራ ዘመን 11ኛ አስችኳይ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ ዳዊት ገበየሁ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሆን የቀረበውን ፕሮፖዛል ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል ።የዳውሮ ዞን ምክር ቤት በአስቸኳይ ጉባኤው በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቀረበውን የሹመት ፕርፓዛል ተቀብሎ አጸደቀ። በተጨማሪም አቶ አስፋው ደሳለኝን የዳውሮ ዞን…

Read More

በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተደረገው የባህር በር ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ወጣቱ ትውልድ በጋራ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ሰብሳቢ ወጣት ይስሃቅ ንጉሴ እንደተናገረው ሀገራችን በታሪክ ወደብ የነበራትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደብ አልባ ሆና መቆየቷን አስታውሰዋል ፡፡ ሀገራችን የወደብ በር ማግኘቷ የገቢና ወጪ ንግድ ስርዓትን ከማሳለጥ ባሻገር የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ወጣት ይስሃቅ ተናግሯል ። በቀጠናው እየተስተዋለ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ከማድረጉም…

Read More

የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገ ሥራ ይጠበቃል:-አቶ አልማው ዘውዴ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በጉድለት የተገመገሙ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወጣቶች ምክር ቤት ተመሰረተ::

ዛሬ በተደረገዉ ምክር ቤት ምስረታ 13 ሥራ አስፈጻሚና 42 የምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል። ምክር ቤቱ ወጣት ይስሃቅ ንጉሴን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ና ወጣት ትህትና ቆጭቶን ምክትል ሰብሳቢ በማድረግ መርጠዋል። በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፡ ገናና የሆነ ሀገር የትክክለኛ ትርክት ውጤት ስለሆነ ብሔራዊነት ገዥ ትርክታችን ሆኖ እንዲገነባ…

Read More

የክልሉ ትምህርት ቢሮ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

በክልሉ የኮንታ ዞን በማህበረሰብና በመንግስት ተሳትፎ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በኮንትኛ ቋንቋ ያሳተመውን ከ64 ሺ በላይ ከቅድመ 1ኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የመማሪያና የማስተማሪያ መፅሀፍት ርክክብ ተደርጓል። በመድረኩ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ምክትል ሀላፊና ስርዓተ ትምህርት ዘርፍ…

Read More