የባህር በር ባለቤትነት ጠቀሜታ በምሁራን እይታ!

Spread the love

የባህር በር ባለቤት መሆን ለአንድ  ሀገር ያለው ጠቀሜታ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ኢኮኖሚን በማሳለጥ እና በሀገራት እና በህዝቦች መካከል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብርን በማጠናከር በኩል ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው፡፡ የባህር በር ባለቤት መሆን የሀገሪቱን ደህንነት ከማስጠበቅ ረገድ ጥቅሙ እጅግ ብዙ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት የባህር በር የነበራት ሀገር በአንድ በታሪክ አጋጣሚ   የባህር በር አጥታ መቆየቷ እሙን ነው፡፡ ሆኖም ግን ሀገራችን ላለፉት 15 ዓመታት የባህር በር ለማግኘት ፍትሃዊ የወደብ ሀብት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ሁኔታዎችን ስታጠን ቆይታለች፡፡

ይህንን ህልም እውን ለማድረግ  ኢትዮጵያ የባር በር በሚታገኝበት ዙሪያ ከሶማሌ ላንድ መንግሥት ጋር ተፈራሪማለች፡፡ ይህ የባህር በር ባለቤት የመሆን ጉዳይ የሀገር ህልውና፣ የደህንነት እና የቀጣይ  ትውልድ ጉዳይ በመሆኑ  መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ምሁራን ሊደግፉት የሚገባ ነው፡፡

በቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የአካዳሚክ፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዲን የሆኑት ዶክተር አህመድ እስማኤል የኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሌ ላንድ መንግሥት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ ተመስርቶ  የተደረሰው ስምምነት እጅግ የሚያኮራ እና የሀገርቱን ኢኮኖሚ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡ አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለዘመን የሰው ልጆች ከቦታው ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ሁኔታ እየበዛ
በመምጣቱ የባህር በር ጉዳይ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ተደርጎ  እየታየ መጥቷል ያሉት ምህሩ እንደሀገር በር ዘግቶ መኖር የማይቻል እና ከሌሎች አፍሪካ ወገኖች ጋር በንግድና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ጋር ለመገናኘት የባህር በር አስፈላጊነት ለጥያቄ አይገባም ስሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በባህር በር ጉዳይ ምሁራን የትኛውንም የሚያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ጠቃሚ የሆነ ሀሳብን ለሌሎች በማስረጽ፣ የውይይት ፎረሞችን በማዘጋጀት እና የተለያዩ የጥናትና ምርምር ተግባራትን በመስራት በኩል ብዙ ሚና መጫወት እንዳለባቸዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሠላም የመኖርን መርህ ተከትለን ከሶማሌ ላንድ ወንድምና እህት ህዝብ ጋር ያለንን የባህል እና የዲፕሎማሲ ትስስር በማጠናከር  የተደረገው ስምምነት ለሁለቱም ሀገራት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አህመድ እስማኤል (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በኮሌጁ የጂኦግራፊ መምህር እና የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ አካዳሚክ ዳይሬክተር አቶ አስረስ አዛዥ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ለብዙ ዓመታት የባህር በር አልባ ሆና ለቆየችው ለሀገራችን ስምምነቱ ተገቢና በርካታ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ይዞ የሚመጣ ነው ብለዋል፡፡ መንግሥት በአመት ለወደብ ኪራይ የሚያወጣዉን ወጪ የሚቀንስ  በመሆኑ ከዚህ አንፃርም ሲታይ ስምምነቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ ከህዝብ ብዛት አኳያ ከአለም አቀፍ ህግም አንፃር ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ ሀሳብ ማንሳቷ እና ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ተገቢ እንደሆነም አንስተዋል፡

ሌላኛው የኮሌጁ ተከታታይ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ተሾመ የባህር በር ስምምነቱ መሳካት መንግሥት ብቻውን ሳይሆን ህዝብና ምሁራን በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ የልማትና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም የወጪና የገቢ ንግድን በማሳለጥ ረገድ የሚኖረው ሚና እጅግ የላቀ እንደሚሆን የጠቀሱት ምሁራኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባር ላይ እንድውል ሁሉም ባለድረሻ አካለት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *