ባለስጣን መስሪያ ቤቱ በቡና ምርት ማሻሻያ ፓኬጅ ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

የቡና ምርት በማሻሻል የቡና አምራች አርሶአደሮችን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የሸካ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ዓለሙ እንደገለፁት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክልሉ ለቡናና ቅመማ ቅመም ምርት ማነቆ የኾኑ ችግሮችን በሳይንስዊ መንገድ በመፍታት ያሉ አቅሞችን ወደ ሀብት ለመቀየር በየደረጃው የተጀመረው ተግባር መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

የቡና ምርትን በመጨመር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ማሳን ማሻሻልና የምርት ማሻሻያ ፓኬጆችን በተገቢው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ በላይ ጎጅአብ የቡና አምራች አርሶደአሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀማመሩ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በክልሉ በቡና ማስፋት ስትራቴጂ በምርት የተሸፈነው የቡና ማሳ ሽፋን ከፊተኛው ቢሆንም በምርት ረገድ እየታየ ያለው ውጤት አናሳ መሆኑ የጠቆሙት አቶ በላይ ጎጅአብ የቡና ምርታማነትን ለማሻሻል በምርት ዘመኑ ምርት እየሰጠ ካለው በ270 ሺህ 500 በላይ ሄክታር የቡና ማሳ ውስጥ 2.2 ከመቶ ማሳ ወይም በቁጥር ደረጃ 6180 ሄክታር ማሳ ቡና በበጀት ዓመቱ ጉንደላና ነቀላ እንደሚከናወን ተናግረዋል።

ከጉንደላና ነቀላ በኃላ ቡናው ተገቢውን ምርት በጊዜ እንዲሰጥ የቡና ማሳ አያያዝና ቁጥጥርን በማጠናከር የተሻለ ምርት ለማግኘት ከ933 ሺህ 367 ቶን በላይ መደበኛ ኮምፓስት ለማዘጋጀት መታቀዱም ተገልጿል።
ተግባር ተኮር የኾነው የአሰልጠኞች ስልጠናው በቡና ጉንደላና ነቀላ እንዲሁም በቡና ገረዛና በበርሚንግ ኮምፓስት አዘገጃጀት ላይ የሚያተኩር ስሆን ስልጠኞቹ ወደ መጡበት ስመለሱ ህብረተሰብን በማስተባበር በምርት ማሻሻያና አዲስ የቡና ዝርያ ተከላ ላይ በክህሎትና በተግባር ያገኙትን እውቀት በማጋራት የተሻለ ምርት እንዲሰበሰብ አስተዋጸኦ ይኖረዋል ተብሏል።
በስልጠናው በአዲሱ የመሬት ለምነት ተክኖሎጂ የኾነው የበርሚንግ ኮምፓስት አዘገጃጀት፣በቡና ገረዛና ጉንደላ እንዲሁም በመደበኛ የኮምፖስት አዘገጃጀት ዙሪያ ከክልሉ ግብር ቢሮ እንዲሁም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፊተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች ስነድ እየቀረበ የሚገኝ ስሆን በስልጠናው ከቀበሌ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ጀምሮ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የቡና ልማትና ጥበቃ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዕድገቱ በዛብህ
