


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የተግባር አፈጻጸም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ነዉ።
በበጀት ዓመቱ ታቅዶ ወደ ተግባር በተገቡና ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ አንኳር ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል።
የክልሉን ህዝቦች የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታትና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰሩ ዋና ተግባራት በዝርዝር ይገመገማል ።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ የተግባር አፈጻጸም ግምገማ ሁሉም አስፈፃሚ ተቋማት የግማሽ ዓመቱን አፈጻጸማቸዉን በማቅረብ እንደሚያስገመግሙ ተገልጿል።
በዕድገቱ በዛብህ
