








በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል።
በዚህም የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የሩሲያው ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዲ .ኤ ሜዴቭዴቭ፣
የካዛኪስታኑ አማናት ፓርቲ እና የሀገሪቱ ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት አባል ሳማት ኑር ታተዛ፣
የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ፣
የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አታ ሰርዳሮቭ እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ያዝጉሊ ማምዶቭ እና የደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ (ኤ ኤን ሲ) ፖርቲ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኖጦሉ ኪይቬት አዲስ አባባ መግባታቸዉን ኢቢሲ ዘግቧል።
